በአንተ ደስ ይለኛል የእኔ ጌታ
ልጽና በመንፈስህ እንዳልረታ
አርቄ እያየሁ ጽድቅ አክሊሌን
በተስፋ እንድጓዝ እርዳኝ ልጅህን
የርስቴ መያዣ መንፈስህ
ያጽናናኝ ሁልጊዜ እንዳልረሳህ
1.
የማትሰለቸኝ የማትረሳኝ
ረዳት ለጉዞዬ ለነፍሴ አጽናኝ
ዓይኔን እንዳላነሳው ከመስቀልህ
ሃሣቤን ጠቅልለው ወደ ሞትህ
ዓይኔን እንዳላነሳው ከመስቀልህ
ሃሣቤን ጠቅልለው ወደ ሞትህ
2.
ዝናህ የገነነው በዓለም ላይ
መቼ ትመጣለህ ፊትህን እንዳይ?
በጣም ጓጉቻለሁ የእኔ ጌታ
ኢየሱሴ እንዳይህ ማራናታ!
በጣም ጓጉቻለሁ የእኔ ጌታ
ኢየሱሴ እንዳይህ ማራናታ!