በኃይሉ ብርታት አሻግሮ
ይኸው ለዛሬ አደረሰን
ጌታ አማላጃች ይመስገን
1.
በአዲስ ዓመት አዲስ ምሥጋና
ለጌታ ኢየሱስ እንደገና
እስከዛሬ ረድቶናልና
በምህረቱ ኖረናልና
2.
እንደምህረቱ ባይሆን ኖሮ
እዚህ ባልተገኘን ዘንድሮ
ነገር ግን ፈጽሞ ያልጠፋነው
ከምህረቱ የተነሣ ነው
3.
በየቦታው ጠላት ሲያጓራ
ከጥፋት ሠራዊቱ ጋራ
ቢያበዛብን ዛቻ ድንፋታ
ድል አገኘን የማታ ማታ
4.
ኃይልን በሚሠጠኝ በርሱ ዘንድ
ያለፈውን እንደ ታሪክ ትተን
ለመጓዝ የረዳን አቤነዘር
ጌታ አማላጃችን ይመስገን