ወደ መነሻ / Back to Home
መዝሙር #276d / Song #276d

ክብር ለአንተ እግዚአብሔር

english translation

ምድብ / Category: ምስጋና / Praise
ደራሲ / Author: unknown
ዓመት / Year: 2025
👁️ Views: 4
1.
የእሥራኤልን ህዝብ የተገዳዳረው
የፍልስጤም ጀግና ጦረኛው
ሲዘንጥ ሲፎክር ዳዊት ተመልክቶ
ወደ ሰልፉ ገባ በአምላኩ ተኩራርቶ
በአንድ ጠጠር ብቻ ጐልያድን ዘረረው
እኛ የምናመልከው ይህን ድንቅ ጌታ ነው
ክብር ለአንተ እግዚአብሔር ክብር ለአንተ (2)
ክብር ለዘለዓለም ይገባሃል
አስደናቂ ጌታ ነህ አይተንሃል
2.
የምድያንም ሰራዊት ቁጥሩ እጅግ ቢበዛም
ከእስራኤል ጭፍራ ጋር ባይመጣጠንም
ጌድዮን ግን በእምነት ወደ ሰልፉ ወጣ
ችቦን አነደደ መለከቱን ነፋ
ምድያም ተዋረደ ሸሸ ከእስራኤል ፊት
ለጌድዮን አምላክ ክብር ይሁንለት
3.
በአህያ መንጋጋ ሺ ሰው የገደለው
ኃይልን የተሞላው ሳምሶን የእግዚአብሔር ሰው
የአንበሳን ደቦል ደፍሮ የገጠመው
በእጁ ብርታት ሳይሆን በአምላኩ ጉልበት ነው
እኛ የምናመልከው ይህን ድንቅ ጌታ ነው
4.
አራት መቶ ሃምሳ የበዓል ነቢያት
ፉክክር ገጠሙ ቀርበው ከኤልያስ ፊት
በእሳት የሚመልስ እርሱ አምላክ ይሁን
በዚህ ሃሳብ ተስማምተው ጀመሩት ጩኸቱን
የኤልያስ አምላክ ነው የመለሰው በእሳት
ለኤልያስ አምላክ ክብር ይሁንለት
100%
100%