ወደ መነሻ / Back to Home
መዝሙር #95 / Song #95

ውለታህ ከብዶኛል የኔ ጌታ

english translation

ምድብ / Category: ምስጋና / Praise
ደራሲ / Author: unknown
ዓመት / Year: 2025
👁️ Views: 1
ፍቅርህ ዳርጐኛል ለእፎይታ
ስምህን ከፍ ላርገው በልልታ
ልስገድልህ ልስጥህ ከበሬታ
ልገዛልህ ከጥዋት እስከ ማታ
1.
እኔንም ከሰው መቁጠርህ
ከቤቴ ገብተህ ማረፍህ
መጐዳቴን ማወቅህ ገርሞኛል
ምን ልበልህ ውለታህ ከብዶኛል
2.
የከፈልክልኝ የደም ዋጋ
ያበረከትክልኝ ግሩም ፀጋ
አድኖኛል ከሞት አደጋ
ዛሬም ግረፈኝ በፍቅርህ አለንጋ
3.
ሁሉም እንዲሰማ የአንተን ዝና
አፌን ልክፈትልህ በምሥጋና
በዜማ ከፍ ላድርግህ በበገና
እስከመጨረሻ እኔም ደጅህ ልጥና
4.
እንደ እኔ የሰራህለት ሰው
ጣፋጭ ፍቅርህን ያቀመስከው
ዘውትር ሲያገለግልህ ቢኖርም
መቼም አይከፋውም ቤትህ አይጠበውም
100%
100%