ወደ መነሻ / Back to Home
መዝሙር #242d / Song #242d

ጌታ ቅደምልኝ

english translation

ምድብ / Category: ምስጋና / Praise
ደራሲ / Author: unknown
ዓመት / Year: 2025
👁️ Views: 3
ጌታ ቅደምልኝ በኑሮዬ ሁሉ
የአንተ ስለሆነ በመከራ ድሉ (2)
1.
ጌታን የሚያስቀድም በኑሮው በቤቱ
አቅፎ እንደ ደገፈው እንደ እናት አባቱ
ያ ነው የአምላክ ወዳጅ ክብሩን የማይፈልግ
በክፉ በደጉ ከቶ ማይበረግግ
2.
በትዕግሥት ጠብቁ አምላክ ይቅደም የሚል
እራሱን በውርደት ከመስቀሉ ሚጥል
ያ ነው ያምላክ ወዳጅ ምኞቱን ያሟላ
ለያዘው ቁም ነገር ከቶ የማይላላ
3.
ጌታ እንድቀድምልህ በኑሮው መከራ
በእምባው እየታጀበ ለመዝሙር ሲጠራ
ያ ነው የአምላክ ወዳጅ ክብሩን የሰቀለ
ያጋንንትን ሥልጣን በእምባው ያቃጠለ
100%
100%