ወደ መነሻ / Back to Home
መዝሙር #46d / Song #46d

ብቻውን ተአምር የሚያደርግ

english translation

ምድብ / Category: ምስጋና / Praise
ደራሲ / Author: ተስፋዬ ጫላ
ዓመት / Year: 2025
👁️ Views: 2
ብቻውን ተአምር የሚያደርግ
ችግረኛውን የሚታደግ
እንቆቅልሽ የሚፈታ
እየሱስ የኛ ጌታ
1.
ጠላት ሲሽቀዳደም ሊመታን በጡጫ
ክንዱን ሰበረልን ሆነልን ማምለጫ
እንናገር ብንል ብዙ እናወራለን
በዚች አጭር ዕድሜ ምሕረቱን ስላየን
በዚች አጭር ዕድሜ ማዳኑን ስላየን
2.
ኃጢአታችን በዝቶ ስንባዝን በዓለም .
ሕይወት ሆነን ኢየሱስ ሊያኖረን ዘለዓለም
ምን እንመልሳለን ከምስጋና ሌላ
በጭንቃችን ሰዓት ለሆነን ከለላ (2)
3.
የአናብስትን አፍ ጥርስ እየሰበረ
ከክብር ወደ ክብር እያሸጋገረ
በደመናው አምድም ዘወትር ይመራናል
ከየሱስ ጋር ሆነን እረ ምን ጐድሎፍል (2)
100%
100%