በፀጋው ዓመታቱንም ደግፎ አስጨርሶናል
ይኸው አዲስ ዓመት ተቀበልን
አሮጌውን አሳልፎን
የሰላም የጤና ይሁንልን /2/
1.
ቀን ሆኖ ማታ ሲተካ ቀን ቀንን እየወለደ
ከሣምንት ሳምንት አለፍን ጊዜያቱ እየነጐደ
ቀናቱ በተራው አልፎ ሳምንቱ በተራው ሄደ
አሮጌው ዘመን ሲያበቃ አዲስ ዘመን ተወለደ
2.
አቤቱ ሥራህ ድንቅ ነው ማነው ቆጥሮ ሚጨርሰው
ማለዳ ማለዳ አዲስ ነው ምህረት ቸርነትህ ብዙ ነው
ተፈጥሮ የሚታዘዘው ጨለማ ብርሃን ሚያደርገው
ሁሉን ቻይ ፈጣሪ የሆነ አምላክ ነው የምናመልከው
3.
ፀሐይ ጨረቃ ከዋክብት ጠፈርን አቆመ በቃሉ
ብርሃን ጨለማ አድርጐ ሁሉን ፈጠረ በኃይሉ
ዘመንም በተራው መጥቶ ዘመንም በተራው ሄደ
አሮጌው ዓመት ሲያበቃ አዲስ ዓመት ታወለደ
4.
አዲስ ሰማይ አዲስ ምድር እንደ ቃሉ እንጠብቃለን
ወደ ዘመን አሻጋግሮን ለክብሩ በሕይወት አቆመን
ዛሬ አዲስ ዓመት ተቀበልን በምድር ሁላችን እያለን
ነገን ሁላችን በሰማይ ለዘላለም እንኖራለን