ወደ መነሻ / Back to Home
መዝሙር #206d / Song #206d

በመዝሙር ውዳሴ

english translation

ምድብ / Category: ምስጋና / Praise
ደራሲ / Author: unknown
ዓመት / Year: 2025
👁️ Views: 3
1.
ቀናትም ያልፍና ዘመን ተፈጽሞ
የክርስቲያን ፈተና በምድር ላይ አክትሞ
በጥፋት ዓለም ውስጥ መኖር ያበቃና
የዐይናችንን እንባ ጌታ ይጠርግና
በመዝሙር ውዳሴ በቅኔ ምሥጋና
በአስራ ሁለት አውታር በታላቅ በገና
ምሥጋና እንልና
ዕልልታው ሽብሸባው በዚያ ይደምቅና
መቼ ቀኑ ደርሶ ጌታም ይከብርና ምሥጋና
2.
መች ይላል ተመስገን ጊዜው ይደርስና
ከልቡ አልቅሶ ለጌታው ይነግርና
ምኞቱም ጥረቱም መቼ ይሳካና
ጌታም ሲል ይሰማል ልጄ ሆይ ተጽናና
3.
አዕላፋት ጻድቃን ከምድር እንሄድና
ነጭ ልብሳችንን ለብሰን ዙፋን እንከብና
ኪሩቤል ላይ ላለው ለበጉ እንሰግድና
መቼ እንዘምር ይሆን ለኤኢየሱስ ምሥጋና
4.
የምድር መጻተኛ ልብህ የተሰቀለ
ስማዕትን ለማየት ተስፋህ ያልጐደለ
መቼ ቀን ሞልቶልህ ጽዮን ትደርስና
ጌታን በዐይንህ አይተህ ልብህ ይረካና
100%
100%