ወደ መነሻ / Back to Home
መዝሙር #38 / Song #38

ደካማና ምስኪን ብሆንም ወራዳ

english translation

ምድብ / Category: ምስጋና / Praise
ደራሲ / Author: unknown
ዓመት / Year: 2025
👁️ Views: 1
ጌታ አይተወኝም በደረቅ ምድረ-በዳ
አሁንም አምላኬን ልቅረብ በምስጋና
ኃይልህ በድካሜ ይፈፀማልና
1.
ድካሜንም አውቆ ድጋፍ የሆነልኝ
መዋረዴን አይቶ ከፍ ከፍ አደረገኝ
የሚያፅናናኝ ወዳጅ መንፈስ ቅዱስ ሰጠኝ
በችግሬ ሁሉ ፈጥኖ ደረሰልኝ
2.
አንደበቴ ደርቆ መናገር ሲያቅተኝ
በችግሬ ጊዜ መፅናናትን ሲሳነኝ
አይኖቼን አንስቼ ጌታን ስመለከት
የሱስ ይረዳኛል ሰምቶ ከሰማያት
3.
ፈተና ሲበዛ ዛሬ በሕይወቴ
እለት እለት አድጐ ቢበዛ ጭንቀቴ
እኔ አልናወጥም ጌታን በመያዜ
በችግሬ ደራሽ ጌታ አለኝ ዘመዴ
4.
የአብረሃምን እምነት ያሰበው ጌታዬ
የኢዮብን ትዕግሥት ያየው መከታዬ
የእኔንም ሕይወት መዝኖ የሚያውቀው
የማይለይ ወዳጅ ሁሌ ከእኔ ጋር ነው
100%
100%