ከሞትም ያድነዋል ከሞትም ያድናል
ከሞትም ያድናል ኢየሱስ።
1.
በሞት ጥላ የሚያድር በግዞት ሸለቆ
ጠላት የሚመታው አሸምቆ
ለአንበሳ መንጋጋ ለጦር የተጣለ
ነበረ ወገኔ የቆሰለ።
2.
ጌታ ደርሶለታል ወንጌል ልኮለታል
ሰማያዊ ብርሐን በርቶለታል
መልዕክተኞች ወጡ ጠላትን ገጠሙ
በመስቀሉ ጉልበት ድል አረጉት።
3.
አለምና ትርፏን ወደ ኋላ ገፍቶ
ከመታወቅ ይልቅ መናቅ መርጦ
ዘሩን ተሸክሞ በለቅሶ የሚዘራ
በደስታ ያጭዳል ካምላክ ጋራ ።