እግዚአብሔርን ብቻ እርሱን መጠበቅ መፍትሔ ያደረገው
ፈጥኖ ደርሶ የሚታደግ ማን አለ እንደ እግ/ሔር
ከትቢያ ላይ የሚያነሳ ሚስኪንን ሚያከብር
1.
አዎን በጊዜው ከፍ እስኪያደርግ ድረስ
ዝም ብለን ከኃይለኛው በታች እንዋረድ
አዎን በጊዜው ከፍ እስኪያደርግ ድረስ
ዝም ብለን ከእግዚአብሔር እጅ በታች እንዋረድ
2.
መርዶኪዎስ ንጉስ ቤት ሥፍራ ተስፋ የቆረጠው
ለእርሱ ብቻ ሳይሆን መዳን ለአይሁድ ካንተ ዘንድ የሆነው
እንቅልፍ ነስተህ ታሪክ ለወጥህ ከውርደት አነሣህ
በሞት ፈንታ ክብርን ሰጥተህ ጠላቱን አዋረድህ
3.
አንተ ያከበርከው ከፍ አድርገህ ሥፍራ የሰጠኸው
በግ ጠባቂ ሳለ አብረህ ሆነህ ከክፉ ያዳንከው
አባቱ እንኳን ትንሽ ያለው የተረሳው ዲዊት
እጅህን ልከህ አነሳኸው ክብርህን ለመስጠት
4.
ክብርን ለማግኘት ዝናን ማትረፍ አዋቂ ለመባል
ለማልቀስ ለመሳቅ ለመዋረድ ጊዜ መቼ ይጠፋል
ባንተ ጊዜ ሁሉ ሆኖ ማየት እንሻለን
ባልከን ነገር ተደስተን ረክተን እንኖራለን