ወደ መነሻ / Back to Home
መዝሙር #75 / Song #75

ነገር ሁሉ ይለወጣል ታሪካችን ይታደሳል

english translation

ምድብ / Category: ምስጋና / Praise
ደራሲ / Author: unknown
ዓመት / Year: 2025
👁️ Views: 1
የምድር ችግር ይረሳል ሁሉም አዲስ ይሆናል
ይታለፋል ይህ ሁሉ እናርፋለን በቅርቡ
ችላ አትበሉ ጠንክሩ የምድር ጣጣን አታስቡ
1.
ማራናታ ቶሎ ና ጌታችን ሆይ ቶሎ ና
ማራናታ ቶሎ ና ተስፋችን ሆይ ቶሎ ና
የምድር ኑሮ ይበቃናል ሰማይ መሄድ ይሻለናል
ነጋ ጠባ ጦርነቱ ሰላም ማጣቱ ከብዶናል
2.
ትላንት ሰላም የነበረው ዛሬ መልኩን ይቀይራል
ጥሮ ግሮ ለመኖር ሲባል ይልቅ የከፋ ይሆናል
ምን ተስፋ አለ የምንጠብቀው በዚች ምድር የምናየው
ጌታ አምላክ ሆይ ቶሎ ና ይህን ጉጉት ናፍቆታችን ነው
3.
አንዱ ሞልቶት ተርፎት ሲኖር ሌላው በራብ ይሰቃያል
ባንዱ በኩል ሲስተካከል ሌላው ደግሞ ክፍት ይሆናል
እጅግ ከፍቷል ይህ አለም ውጣውረዱ አሰቃየን
ማራናታ ጌታሆይ እንባችንን አብስልን
4.
በአዲስ ምድር በደስታ እንድንኖር በእፎይታ
ሀሌሉያ ዝማሬ እንድናዜም በእልልታ
እንደፀዳል እያበራን እንድናቀርብ ምስጋና
የቅዱሳን ብሩህ ተስፋ ጌታ ኢየሱስ ሆይ ቶሎ ና
100%
100%