እግዚአብሔር ኃያል በስልፍም ደግሞ ኃያል
ከቶ እስከዛሬ በማን ተረቶ ያውቃል ።
1.
ሕዝቡን ከልሎ የሚዋጋ
ለጠላት ዛቻ የማይሰጋ
ብድራት መላሽ የኛ አምላክ
ይረታ እንጂ መረታትን
2.
የእምነት ባለድል ሳይጸጸት
ጌታውን አምኖ ሳያፍርበት
ለተስፋውም ለብሶ ስንስለት
ሕይወቱን ስጥቷል ሳይሰስት (2)
3.
አንተም በኃይሉ ድል ነስተህ
በእቶን ተፈትነህ ነጥረህ
ለመንግሥቱ ብቁ ሆነህ
እንድትወጣ ጌታ ይርዳህ (2)
4.
ያን ጊዜ ተዋግቶ የረታ
የጠላቱን ጅማት የፈታ
በጽኑ አመታት የሚመታ
ሁሉን የሚችል የድል ጌታ (2)