በምሥጋና ሆ!
በምሥጋና ድል ይገኛልና (2)
1.
ሸለቆ አሽቆልቁለው ሲያለቅሱ
ሰዎች ለምሥጋና ቢነሱ
በሐዘኑ ፈንታ ደስታ
በለቅሶውም ምትክ ዕልልታ
2.
አይዞህ የሚል ቃላት ሲጠፋ
ጭው ካለው በረሃ ሲደፋ
ውኃ ጥም ሲተካ በእርካታ
ምሥጋና ሲታጀብ በሆታ
3.
ሰማያት እንደ ናስ ሊዘጉ
በምሥጋና ሕይወት ቢጠጉ
ያንዣበበው ጥላ ሲገፈፍ
አመስግኖ በአምላክ መደገፍ
4.
ብቅ ሲል ካለበት ሸለቆ
ፊቱ ፈገግ ሲልም ስቆ
የጮኽበት ጥሪ ተሰምቶ
በምሥጋና ሆ ሲል እረክቶ