ማነው ዛሬ የሚያስተናግደኝ
ከርሱ ጋራ እገባለሁኝ
እራቴንም እበላለሁኝ
1.
ምጻቱ ደርሶ የሚተጋ ሰው
ሲጠራ አቤት እነሆኝ የሚለው
እርሱ ነው ታማኝ የጌታ አገልጋይ
በእግ/ርም ቃል እጅግ አሰተዋይ
2.
ትዕዛዝ ጠብቆ ተግባርን ሁሉ
ነጩን ልብስ ለብሶ ሁሉም በቃሉ
እርሱ ነው ቅዱስ ታማኝ የተግባር ሰው
ለእግ/ርም ታዛዥ መልስም ሰጭ ሰው
3.
ሰዎች አስተውሉ የጊዜውን መምጣት
ብርሃንን ፈልጐ የሚያደርስ ከእውነት
እውነትንም ይዞ የፀና በእምነት
በሩንም ይከፍታል ይድናል ከሞት
4.
ወርቅ ይዞ ሲመጣ የሚቀበል
ኩል ይዞ ሲመጣ የሚቀበል
እርሱ ነው ታላቅ ፍፁም የተግባር ሰው
ፍፃሜውም ደግሞ እጅግ ያማረ ነው
5.
መለዕክት ያለው ቃሉን መርማሪ
ጊዜውን የሚያውቅ ጥሩ አስተማሪ
እርሱ ነው ቅዱስ መለከት ነፊ
ታማኝ እረኛ ነፍሳት አትራፊ