ወደ መነሻ / Back to Home
መዝሙር #284d / Song #284d

ክርስትናዬ ጠቀመኝ

english translation

ምድብ / Category: ምስጋና / Praise
ደራሲ / Author: unknown
ዓመት / Year: 2025
👁️ Views: 3
1.
ከእግዚአብሔር ጋራ ተጓዳኝ
ቢያገኝም ቢያጣም አመሥጋኝ
ቢወድቅም እንኳን ይነሳል
ምርኮው ይመለሳል
ክርስትናዬ ጠቀመኝ
ውሎ እያደረ ጣፈጠኝ
2.
በሃዘን ጊዜ ደስታ
በለቅሶ ምድር ዕልልታ
በረሃብ ዘመን ጥጋቤ
ኢየሱስ ነው ገንዘቤ
3.
የዓለም ኑሮ መራራ
ያልጠረበ ሸካራ
የለቅሶ አገር የዋይታ
በቃህ አለኝ ጌታ
4.
በጀሮ ስሚ ያወቅሁት
በግል ሕይወቴ አየሁት
ከቀን ወደ ቀን ደመቀ
ቤቴን እያሞቀ
100%
100%