ኃጢያታችሁ ቀልታ እንደደም ብትመስል
እጅግም ቢጠቁር ጥላሸት ቢመስልም
በደላችሁ በዝቶ ፅዋውን ቢሞላም
ተናዞ የተዋት ይቅርታን ያገኛል
ንሠሀ የገባ ምህረት ይሠጠዋል
ከልተመለሰ ግን በኃጢያቱ ይሞታል x2
1.
ተነሱ ወደጽዮን እንሂድ ወደምላካችን
ግርማ ክብራችን ጠፍቶ ቢቀርም አጥንታችን
ወደ እግዚአብሔር እንቅረብ ይመለሳል ክብራችን
ያደርግልናል እየሱስ የድል አክሊል በራሳችን
2.
እነሆ እንደተስፋ ቃሉ ጌታችን ሊመጣ ነው
እስካሁንም የዘገየው ያንተን መምጣት ሲጠብቅ ነው
ተው ተመለስ ልጄ ና ይህ ወርቃማ ጊዜህ ነው
የምህረት በር ከተዘጋ ማንም አይችልም ሊከፍተው
3.
ወደ ልዑል እግዚአብሔር በቶሎ እንመለስ
ኑ ከጠላት ሥብራት በጌታ እንፈወስ
እሺ ብትሉ ብትመጡ በረከት ታገኛላችሁ
እምቢ ብላችሁ ብትቀሩ በሠይጣን ትጠፋላችሁ
4.
እግዚአብሔር ኑ እያለ በፍቅር ጥሪው ይጠራል
እጆቹን ዛሬም ዘርግቶ ቆሞ እናንተን ይለምናል
ኃጢያታችሁን ተናዘዙ ጊዜው አልቋል ተመለሱ
እግዚአብሔር ሲጣራ ስሙት በንሥሀ ተመለሱ