ወደ መነሻ / Back to Home
መዝሙር #326d / Song #326d

ደሙን ለእኔ አፍሶ አዳነኝ

english translation

ምድብ / Category: ምስጋና / Praise
ደራሲ / Author: unknown
ዓመት / Year: 2025
👁️ Views: 3
1.
ኮብልላ ነበረች ነፍሴ ከእግዜር መንገድ
በጣም የበደልኩኝ ኃጢአተኛም ነበርኩ
ግን አዳኜ ከላይ ፍቅሩን ሰጠኝ ሰላም
ልጁን ለእኔ ልኮ አወጣኝ
ደሙን ለእኔ አፍሶ አዳነኝ (2)
የማልረባም ብሆን
አምላኬን የማላውቅ
ልጁ ለእኔ ወርዶ አወጣኝ
2.
ተስፋ ቢስ ነበርኩኝ ሊያወጣኝ ሲመጣ
ግን እርሱ ነገረኝ ነጻ እንደምወጣ
ከዚያማ አነሳና ክብሩን አቀዳጀኝ
ልጁን ለእኔ ልኮ አወጣኝ
3.
ልቤን ደስ ይለዋል ከመረጥኩት ወዲህ
ከማዕበሉ አሁን ወደርሱ ሸሻለሁ
ክንዱን ከተደገፍኩ አልፈራም መከራን
ልጁን ለእኔ ልኮ አወጣኝ
4.
ሰማያዊ ደስታን ሰላምን ከሰጠኝ
ጌታ ሆይ ሕይወቴን ለአንተ ሰጣለሁኝ
እንግዲህ እጄን ያዝ ከአንተም ጋር አቁመኝ
ልጁን ለእኔ ልኮ አወጣኝ
100%
100%