ጌታን በማገልገል ሳይቀደስ ሕይወት
አይገኝም በእውነት የሰማዩ መንግሥት
ቀኑ ሳለ ተመለስ እንዳትጠፋ በእሳት
1.
ክፋት በምድር ላይ ሲስፋፋ እያየህ
የሰይፍ የጦር ወሬ ዘውትር እየሰማህ
ተነሳ ወንድሜ ከእንቅልፍህ ንቃ
በምድር ላይ መንከራተቱ ቶሎ እንዲያበቃ
2.
ጠላት ተሰልፎ በዙሪያህ ሲያገሣ
ከምድር ገፅ ሊያጠፋህ በቁጣ ስነሣ
እንዴት ዝም ትላለህ ገሻ ጦርህን አንሣ
ጌታ ከጐንህ ነውና አትፍራ ተነሣ
3.
ከክፉ ጠላት ዛቻ ሁሌ የሚጨነቁ
በችግር በመከራ ሌተቀን ሚሳቀቁ
ጌታን ተቀብለው ወደ ጉያው እንዲገቡ
አዋጅን አሰማ ለእውነት እንዲታዘዙ
4.
መንገዱ ጠባብ ነው ጉዞውም ጠመዝማዛ
ችግር ስቃይ መከራ እጅግም የበዛ
ቢሆንም ይዘለቃል ይገፋል ያ ሁሉ
እርሱ ይደግፍኃል በማይደክመው ኃይሉ