ወደ መነሻ / Back to Home
መዝሙር #332d / Song #332d

ላይህ እናፍቃለሁ

english translation

ምድብ / Category: ምስጋና / Praise
ደራሲ / Author: unknown
ዓመት / Year: 2025
👁️ Views: 4
1.
ብርሃን ብርሃኔ ለእኔ ሆኖ
በመንገዴ አንተን እያየሁ
ያወጅኩትን ሞትህን ቀምሼ
በትንሳኤ ልምሰልህ እርዳኝ
ላይህ እናፍቃለሁ
ጌታ እናፍቅሃለሁ
ላይህ እናፍቃለሁ ጌታዬ
የእጆችህን ቁስል
የእግሮችህን ቁስል
የተወጋው የቀኝ ጐንህን
2.
እንባዬ ይሰማህ ከዙፋንህ
ብሩህ ሗህንም ሰንጥቆ
ነፍሴ የምታርፍበት አጣች ጌታ
መቼ ነው የማይህ ስትመጣ
3.
ሁሉን ለመፈጸም ጌታ ሲታይ
ክብሩን አንሠራፍቶ በሰማይ
ልጆቹን ለመንጠቅ ሲልክ እጁን
ምን ስሰራ ያገኘኝ ይሆን
4.
በተጠራ ጊዜ ቃሌን ሰምቶ
ያልጠበቀኝ በጊዜው ነቅቶ
ዕድሉን ያጐድላል ብሏልና
ነፍሴ ሳትደክም ጌታዬ ሆይ ና
100%
100%