ወደ መነሻ / Back to Home
መዝሙር #138d / Song #138d

እንግዳ ነኝ እኔ ስኖር በዚች ዓለም

english translation

ምድብ / Category: ምስጋና / Praise
ደራሲ / Author: (ማኅሌተ ለእግዚአብሔር-1963)
ዓመት / Year: 2025
👁️ Views: 2
1.
እንግዳ ነኝ እኔ ስኖር በዚች ዓለም
ሀብቴም በሰማይ ነው ከዚህ ምንም የለኝ
መላእክት ይጠሩኛል ከሰማይ በር ከፍተው
ከእንግዲህ ይህ ዓለም ፍጹም ቤቴ አይደለም።
ታማኝ ወዳጅ እንዳንተ እንደሌለኝ
ጌታ ሆይ ታውቃለህ እኔን የሚያጽናናኝ
መላእክት ይጠሩኛል ከሰማይ በር ከፍተው
ከእንግዲህ ይህ ዓለም ፍጹም ቤቴ አይደለም።
2.
ወደ ፊት ልራመድ ይጠባበቀኛል
የሱስ ይቅር ብሎኝ በሩን ከፍቶልኛል።
ምንም ድሃ ብሆን እኔን አይተወኝም
ከእንግዲህ ይህ ዓለም ፍጹም ቤቴ አይደለም።
3.
አፍቃሪ አዳኝ አለኝ በላይኛው አገር
ናፍቆቴን አልተውም ፊቱን እስካይ ድረስ
በሰማይ ደጅ ቆሞ ይጠባበቀኛል
ከእንግዲህ ይህ ዓለም ፍጹም ቤቴ አይደለም።
4.
በላይኛው አገር በአንድነት እንኖራለን
ከቅዱሳን ጋር በድል እልል እያልን
የተወጋውን በግ በዓይናችን እያየን
ባልተሰማ ዜማ ክብሩን እንገልጻለን።
100%
100%