ወደ መነሻ / Back to Home
መዝሙር #78 / Song #78

ለሰዎች በደልና ኃጢያት ብሎ

english translation

ምድብ / Category: ምስጋና / Praise
ደራሲ / Author: unknown
ዓመት / Year: 2025
👁️ Views: 1
ወደ ምድር የወረደው ክብሩን ጥሎ
ተሰቃይቶ ተቸግሮ የተገፋው
ከእንግዲህ ግን በድል ከብሮ ነው ሚመጣው
1.
አዋጁ ተነግሮ በምድር ላይ
መለከት ሲነፋ ከሰማይ
በክብር ሲመጣ ጌታችን
እንዘምራለን ሁላችን
2.
ድል አድርጐ ጠላታችን ያሳፈረው
ከብሮ ሊነግሥ ከሞት በድንቅ የተነሣው
በሰማያት የከበረው ልቀ-ካህን
የመንግሥት ዘውድ ይጭናል ሲመጣልን
3.
ሰማያዊ መቅደስ በጢስ ይሞላና
የማማለድ የፍርድ ሥራም ያበቃና
ተፈፀመ የሚለው ድምጽ ይነገራል
የነገሥታት ንጉሥ የሱስ ይገለፃል
4.
ካመንንበት ጊዜ ይልቅ ይኸው ዛሬስ
መዳናችን እጅግ ቀርቧል እኛም ሊንነግሥ
ስለዚህም ምልክቱን አስታውሰን
ተዘጋጅተን እንቆየው ጌታችንን
5.
ላመንንበት ለሚንወደው ለልጆቹ
የደስታ ቀን የሀሴት ነው መገለፁ
ለአመፀኞች ግን ጨርሶ ላላመኑት
ይሀዘን ነው የመንቀጥቀጥ የዋይታ ዕለት
100%
100%