ወደ መነሻ / Back to Home
መዝሙር #18 / Song #18

በሀጢያት እንዳንሞት ሁሉንም ታግሷል

english translation

ምድብ / Category: ምስጋና / Praise
ደራሲ / Author: unknown
ዓመት / Year: 2025
👁️ Views: 1
በሰዎች መካከል መናቁን ችሎታል
ቢሞትም ስለኛ ድል አርጐ ተነስቷል
የሰይጣንን መንግሥት የሱስ አናውጦታል
1.
መቃብር ፈንቅሎ ከሙታን መካከል
ተነስቷል /2/ ጌታ ተነስቷልጠላት ተሸንፎ ህይወት አግኝተናል
ጌታ ተነስቷል
2.
በትንሳኤ ማልዶ ጌታችን ተነስቷል
አሻናፊው የሱስ ማንስ ይመስለዋል
ሁሉን ድል አድርጐ በህይወት ይኖራል
የሲኦል መክፈቻ ቁልፉን በጁ ይዟል
3.
በየሱስ ድል መንሣት ጠላታችን አፍሯል
ይከስ የነበረውን አፉን አስይዞታል
ለኛም ለልጆቹ ቃልን ገብቶልናል
እርሱን በትንሣኤ እንድንመስለው ወዷል
4.
ሲኦል የከደነው ምድር የሸፈነው
አይደለም የኛ አምላክ መቃብር ያስቀረው
መላዕክት ብለዋል ህያው ነው ህያው ነው
እኛም እንላለን ህያው ነው ህያው ነው
100%
100%