ወደ መነሻ / Back to Home
መዝሙር #135 / Song #135

በማይለቅ እጅህ እጃችንን ያዘን

english translation

ምድብ / Category: ምስጋና / Praise
ደራሲ / Author: unknown
ዓመት / Year: 2025
👁️ Views: 1
በዚህ ክፉ ዘመን በክንድህ ደግፈን
አቤቱ ጌታችን ባንተ ተማምነናል
እስከ ግብ አድርሰን ሁሉ ይቻልሃል
1.
ጉልበታችን ዝሎ ኃይላችን ተሟጦ
መንፈሳችን ደክሞ እንዲሁም መንምኖ
በከንአን አፋፍ ሆነን ተስፋ እንዳንቆርጥ
አባት ሆይ አጽናናን ኃይልህን ላክልን
2.
በምነቱ ጽኑ ታማኝ ኮከብ የመሰለ
በኃይማኖት ጀግንነት ስሙ የተጠራው
ቀስ በቀስ እምነቱን ሲተውና ሲክድ
እኛንም አስፈራን ይህ የጽዮን መንገድ
3.
ከሰው ታማኝ የለም ምንተማመነው
ከጽዮን ያደርሰናል ጽኑ ነው ምንለው
ታማኙ እረኛችን አንዴም የማትረሳን
አንተ ነህ አዳኛችን ቤታችን አድርሰን
4.
የቆሙ የመሰሉ ሥፍራውን ሲለቁ
ከቦታው መተው ሲተኩ በሰው የተናቁ
ትንቢቱ ሲፈፀም አየን በዐይናችን
በስም ብቻ እንዳንቀር አስበን ጌታችን
100%
100%