ወደ መነሻ / Back to Home
መዝሙር #81 / Song #81

ልንቀበል ያለው ብሆንም መከራ

english translation

ምድብ / Category: ምስጋና / Praise
ደራሲ / Author: unknown
ዓመት / Year: 2025
👁️ Views: 1
እግ/ር ይለናል በፍፁም አትፍራ
ሁሉንም ካለፍን በድል ከተሻገርን
የአሸናፊን ዋጋ አክሊል እንወስዳለን
1.
የሕይወትን አክሊል ከእጁ እንድንቀበል
እስከሞትም ድረስ የታመን እንሁን /2/
2.
በእሳት ውስጥ አልፈን ነፍሳችንን ስጥተን
እስከሞትም ታምነን በጌታ ከፀናን
በትንሣኤ ጠዋት እድል ይኖረናል
ከፃድቃን ጉባኤ ዕጣችን ይሆናል
3.
ስደቱን ተጋፍጠን ችግሩንም አልፈን
ለማለፍ ከበቃን በአለቱ ላይ ፀንተን
ስለ እምነታችን ጌታ መስክሮልን
የተስፋዋን ምድር እንገባባታለን
4.
ከግብፅ ብዙ ገንዘብ ከፈርኦን ጮማ
ከኢየሱስ ጋር መኖር ይሻለናልና
ብለን ተቀብለን ግብፅን በቀን ወጥተን
ከእግ/ር ሕዝብ ጋር ፅዮን አንገባለ
100%
100%