ደረቁን ምድረ በዳ ምን ተስኖት
የሞላዋል በአበባ ምን ተስኖት
የጐደለኝን ሁሉ ምን ተስኖት
ያደርግልኛል ሙሉ ምን ተስኖት
ለእርሱ የሚያቅት የለም
ይችላል እርሱ ዘለዓለም (2)
ሁሉን ቻይ ነውና
እናክብረው በምሥጋና
1.
የሞተውን እሬሳ ምን ተስኖት
እናያለን ሲያስነሳ ምን ተስኖት
ለእኛ ያቃተን ሁሉ ምን ተስኖት
ይቻለዋል ለእርሱ ምን ተስኖት
ኤልሻዳይ አምላክ ነውና
የሚሳነው የለምና
ምን ተስኖት እንበለው (2)
ድል የሚገኘው ያኔ ነው
2.
ጐልያድን የዘረረ ምን ተስኖት
ባሕሩንም የከፈለ ምን ተስኖት
የፈርኦንን ሠራዊት ምን ተስኖት
አርጐታል የውኃ ራት ምን ተስኖት
ከአቅማችን በላይ ከብዶ
የሚረዳን ወገን ጠፍቶ
ምን ተስኖት ግን ይደርሳል (2)
ከጐናችን ሆኖ ይቆማል
3.
ደምና ባይታይም ምን ተስኖት
ነፋስም ባይነፍስ ምን ተስኖት
ሸለቆውን በውሃ ምን ተስኖት
ይሞላዋል የእኛ ጌታ ምን ተስኖት
ለሰው የማይቻለው
ለእርሱ ብቻ የተቻለው
ሁሉን ነገር ያደርጋል (2)
ምን ተስኖት ይቻለዋል