ወደ መነሻ / Back to Home
መዝሙር #328d / Song #328d

እስከምንገናኝ በሰመዩ መቅደስ

english translation

ምድብ / Category: ምስጋና / Praise
ደራሲ / Author: unknown
ዓመት / Year: 2025
👁️ Views: 4
እስከምንገናኝ በሰመዩ መቅደስ
አንተ መሪ ሁነኝ በተስፋ ልገስግስ
እለት እለት ጌታ በመንፈስ ልታደስ
1.
በእንባ ውቅያኖስ በተስፋ ጀልባ ላይ
ምልክት ስጠብቅ ሰማይ ሰማዩን ሳይ
በተፈተንኩ ቁጥር ችግር ስበዛብኝ
ማጉረምረም ሰለችኝ ጌታ ሆይ ናልኝ።
2.
አንዱን ስለው አንዱ እየከሸፈብኝ
ተጨንቄአለሁ አምባዬ ገላግለኝ
በክብር ዙፋን ላይ ጌታ ተሞሽረህ
የሰርገኛ ልብሴን ጥራኝ አዘጋጅተህ
3.
በናፍቆት ነውዤ ስቅል ላላው ልቤ
መቅኖ ብስ ለሆነው ውጥንቅጥ ሀሳቤ
መሳሪያ አብጅለት ልገላገል እኔ
እፎይ ብዬ ልኑር ተገለጽ መድህኔ
100%
100%