አምላካችን መቼ ዋሽቶ ያውቃል
እንደተስፋ ቃሉ ቶሎ ይመለሳል
እናውጅ አዎን ይመጣል
1.
ለአህዛብ ማዳኑን እናብስር
የምሥራቹን ቃል እንናገር
የእምነት ችቧችንን እያበራን
በጨለማ ላሉት ብርሃን እንሁን
2.
ወገኖች እስኪ እናስተውል ዘመኑን
በጌታ መምጫ ቀን ፀፀት እንዳይሆንብን
ቀን ሳለን ዛሬ ኃጢያታችንን ተናዘን
ንስሀ እንግባ ጊዜው እንዳለቀ አውቀን
3.
የጌታችን ምፃት እጅግጉን ተቃርቧል
የተፃፈው ትንቢት ሲፈፀም ይታያል
እንግዲህ ጊዜውን ነቅተን እንጠብቅ
በክብር ሲገለጥ በአየር ልንነጠቅ
4.
በዘላአለማዊ ክንድህ ደግፈን
በፊትህ እንድንቆም በፀጋህ አኑረን
ለዚያ ታላቅ ቀናትህ አብቃንና
እናውድስህ በክብር ምስጋና