ቤቱን የሚያድስ እንደነህምያ
በዚህ ዘመን ለእውነት ታጋይ
እንደ ኤሊያስ ቆራጥ አገልጋይ
1.
ጊዜውን ጉለበቱን ለአመላክ ክብር
መስዋዕት ያረገው ሁሉን ነገር
እርሱ ማነው ታማኝ ባሪያ
ለእውነት የሚቆም እንደነህምያ
2.
ጌታ ሆይ ለህዝብህ ራራ የሚል
ምህረትን ለመንጋው የሚለምን
ልቡን አቅንቶ ወደ ላይ የሚያይ
ታማኝ ካህን ማነው የሚጸልይ
3.
ለጽድቅ ሚራብ እንደ ጳውሎስ
ለእውነት ታጋይ እስከ ግብ ድረስ
በአምላክ ቤት ለሚሠራው እርኩሰት
የሚያነባው ማነው ለህዝቡ ጥፋት
4.
ባየውና በሰማው ቃል
በተረዳው በእውነት ወንጌል
ጸንቶ የሚቆም እንደ አለት
እርሱ ማን ይሆን ጌታ ሚመካበት
5.
ቀንና ሌሊት ለአምላክ ሥራ
ደከመኝ ሳይል የሚሰማራ
የክርስቶስ ልብ ያለው እርሱ ማነው?
ለነፍሳት ደህንነት የሚተጋው