ወደ መነሻ / Back to Home
መዝሙር #2 / Song #2

አስተዋይ የሆነ ማንም ሰው ቢኖር

english transilation

ምድብ / Category: ምስጋና / Praise
ደራሲ / Author: unknown
ዓመት / Year: 2025
👁️ Views: 8
አስተዋይ የሆነ ማንም ሰው ቢኖ
አንዴ ቆም ይበልና ዘመኑን ይመርምር
አለም በክፋት ላይ ክፋትን ሲጨምር
ሰው ክብርን ሲያጐድል ለእግዚአብሔር
ምንጠብቀው ምን አለ ከምጻቱ በቀር
1.
ምን ልዩነት አለ ዘመን እንደድሮው ነው
የወደድኩትን ሁሉ ዛሬም አደርጋለሁ
የምትል አንተ ሰው ተው ይሻልሃል
በእግሩ ሥር ውደቅ ና አለም ይበቃሃል
2.
እርካታ የሌለውን ጥቅም ስታባርር
ሁሌ ስታበጃጅ የራስህን ክብር
አንዴም ሳታስተውል ጊዜው መድረሱ ነው
ሳትዘጋጅ ቢመጣ ወዴት ልትገባ ነው
3.
ጊዜውን እስቲ እይ በደንብ መርምረው
የአለም መድረሻስ እስከ ወዴት ነው
ባይንህ ስታይ ኧረ ጥፋት መምጣቱ ነው
አትዘገይ ቶሎ ና በሩ ሊዘጋ ነው
4.
የሚታየው ሁሉ ከቶ አያረካህም
ከኢየሱስ በቀር እረፍት አይገኝም
ስለዚህ ወዳጄ እስቲ ቃሉን አስተውል
ተስፋህን ካሁኑ አጽና ምፃቱ ተቃርቧል
100%
100%