ወደ መነሻ / Back to Home
መዝሙር #142 / Song #142

እንዴት ወደድከኝ ጌታ /2/

english translation

ምድብ / Category: ምስጋና / Praise
ደራሲ / Author: unknown
ዓመት / Year: 2025
👁️ Views: 1
አሣ አጥማጁን ሰው እንዴት አሰብከኝ
እጅግ ገርሞኛል ጌታ አመራረጥህ
እኔም ደረሰኝ ይሄ ድንቅ ማዳንህ
1.
እኔም አውቃለሁ ኃጢያተኛ ነኝ
እንደሥራዬ ቢሆን ሞት የሚገባኝ
በደማስቆ መንገድ ድንገት አገኘኝ
አይኔን አበራህ ሃንያን ልከህ
2.
እጅግ የተማሩ አውቀናል ሚሉ
ባለም ዙሪያ ሞልቷል አልጠፉም አሉ
ከደሳሳ ጐጆ እኔን መምረጥህ
ኧረ ደነቀኝ ጌታ አደራረግህ
3.
በኃይል በጉለበት አላስገደድከኝ
በፍቅር ብቻ ጌታ እኔን ማረከኝ
እኔም ተሸነፈኩና ተከተልኩህ
ከትላንት ይልቅ ዛሬ እጅግ ወደድኩህ
4.
ብርሃን ቸርነትህ ለኔ ብዙ ነው
ስንቱን እቆጥራለሁ እጅግ ድንቅ ነው
ከትቢያ አንስተህ ታስደንቃለህ
እኔስ እልሃለሁ አንተ ልዩ ነህ
100%
100%