ወደ መነሻ / Back to Home
መዝሙር #204d / Song #204d

ምሥጋና ምሥጋና ምሥጋና ምሥጋና

english translation

ምድብ / Category: ምስጋና / Praise
ደራሲ / Author: ታምራት ኃይሌ
ዓመት / Year: 2025
👁️ Views: 4
ምሥጋና ምሥጋና ምሥጋና ምሥጋና
ከአዕምሮአችን በላይ ለሆነው ውለታ
ቆጥረን እስከማንደርስ ለበዛው ስጦታ
እናከብርሃለን ክበርልን ጌታ
1.
አሳዳጃችን ከባሕር ሰጥሞ
ምድረ በዳችን ባንተ ለምልሞ
ከያለንበት ተሰብስበናል
እኛም ሰው ሆነን ሰውን ማርከናል
2.
በሰው ልጅ ኃጢአት ምድርን ብትቀጣ
የመከራ ጐርፍ ከላይ ቢመጣ
በዙሪያችን አጥር ሰርተሃል
ለእኛ ለሕዝብህ መርከብ ሆነሃል
3.
የፈርዖን ጦር ሕዝቡን አሳዶ
እርሱ ግን ቀረ ከባሕር ማዶ
እርስታችንን በድል ወርሰናል
በአንተ እረኝነት እዚህ ደርሰናል
100%
100%