ወደ መነሻ / Back to Home
መዝሙር #56d / Song #56d

ከልጅነት እስከ ሽምግልና

english translation

ምድብ / Category: ምስጋና / Praise
ደራሲ / Author: ጌጃ ቃለ ሕይወት ቤ/ክ «ሀ» መዘምራን
ዓመት / Year: 2025
👁️ Views: 3
1.
ከብላቴንነት እስከ ሽምግልና
አደራ ለሰጠው ተሸከመኝ ላለው
ጌታ ታማኝ ነው አደራውን ጠብቋል
መቼ ይደክማል በማን ተረቶ ምርኮን ያጐላል።
ከልጅነት እስከ ሽምግልና
እግዚአብሔር ይሸከማልና
ለስሙ ይሁን ምስጋና (4)
2.
በልዑል መጠጊያ ተጠግቶ የሚኖር
ሁሉን በሚችለው አምላክ ጥላ የሚያድር
ዘሩ ለምልሞ ምድርን ይወርሳል
ጌታ ታማኝ ነው ለታመኑበት ክብር ይሆናል።
3.
የአብርሃም አምላክ እርሱ የባረካቸው
በዘለዓለም ኃይሉ ያበለጸጋቸው
የጌታን ክብር ግርማውን ያወራሉ
ክብር ለስሙ ለዘለዓለም ይሁን ይላሉ።
100%
100%