ወደ መነሻ / Back to Home
መዝሙር #86 / Song #86

ዛሬም የዚህ ዓለም ገዢ ሆይ የምልህን በርግጥ ስማ

english translation

ምድብ / Category: ምስጋና / Praise
ደራሲ / Author: unknown
ዓመት / Year: 2025
👁️ Views: 1
የእቶን እሳቱም ቢጨምር የቁጣህ ድምፅህ ቢሰማ
ላቆምከው ለወርቁ ምስል በጭራሽ ወድቄ አልሰግድም
ስለዚህ ቁጣህ ገንፍሎ እሳቱ እጥፍ ቢነድም
አምላኬ በቁጣህ እሳት እንድጠፋ ከቶ አይፈቅድም
ባይድነኝ ብሞት እንኳን እኔ ግን ለአንተ አልሰግድም /3/
1.
ዛሬም ፊትህ ምስል ቆሟል ትዕዛዛቱን እንድትጥስ
ገንዘብን ሀብትን በመውደድ የአምላካችን ቤት እንዲፈርስ
ከምኞት ከስስት ስርቆት ከክፉ ሥራ ውጣና
ጣላትህን ኑረህ አሳየው በእምነትህ ፀንተህ ቁምና
2.
ዛሬም ፊትህ ምስል ቆሟል የጌታን ሰንበት ለማፍረስ
በሰንበት ለአምላክ እንዳንሰግድ በሥራ ሕጉ እንዲፈርስ
ሰንበትን በቅድስና ጠብቀው ታማኝ ሁንና
ጠላትን በእምነት ተቋቋም ባይማኖት ፀንተህ ቁምና
3.
ዛሬም ፊትህ ምስለ ቆሟል በዘር ጐሣ መተራመስ
ወገኔ ይህንን አስተውል አንድ ነን በጌታ የሱስ
ሰይጣን ሆይ ከእንግዲህ እፈር ከምድር ጉዳይ የለንም
ዘር ጐሣ እየቆጠርን በሥጋ አንለያይም
4.
ዛሬም ፊትህ ምስል ቆሟል እግዚአብሔርን እንድትክድ
5.
አውሬው በቁጣ ተነስቷል ሊያርቅህ ከእውነት መንገድ
እግዚአብሔርንም አክብሩት ትዕዛዛቱንም ጠብቁ
ላውሬው እና ለምስሉ ከመስገድም ተጠንቀቁ
100%
100%