1.
ጌታችን አመስግኑት
በደስታ ዝማሬ
ሕፃናት ያመስግኑት
የሱስ ጌታችንን
ታናሾችን ወደደ
ወደርሱም ጠራቸው
በክንዱም አቀፋቸው
ነፍሱንም ሰጣ ቸው
2.
ጎልማሶች ያመስግኑህ
ቅኔም ይቀኙልህ
ንጹህ ያለ ኃጢአት
በምድር የነበርህ
መታዘዝ አስተምረን
ክፉን እንድንሸሽ
በሰማያዊ መቅደስ
ካንተ ጋር እንድንሆን
3.
ሴቶችም ያመስግኑህ
አንተ የድንግል ልጅ
ጸጋና ትህትና
ሕይወትህን የሞላ
ጸጋህን አልብሣቸው
ሰላምህን ስጣቸው
በፊትህ የሚያበራ
እምነት ላክላ ቸው
4.
በአንድነት ተባብረን
ላንተ እንቀኝልህ
ብርሃን መሪ ሁንልን
በልጅነታችን
ወደላይም ምራን
በምድር ላይ ሣለን
እንዳንተ እንድንሆን
በጥበብህ አድገን