ምሥጋናውን ሁሉ በጭራሽ አትርሺ
ይቅር የሚል ጌታ በሙሉ ኃጢአትሽን
አምላክ አለሽና ማረፊያ የሚሆን
1.
ሰዎች በህመሜ ሸሽተው ሲፀየፉኝ
እርኩስ እርኩስ እያልክ ብለው እለፍ ሲሎኝ
ብትወድስ ትችላለህ ብለው ልታነፃኝ
እወዳለሁ ልጄ አለና ደሰሰኝ
}x2ከለምጽ አንጽቶኛል የናዝሬቱ ኢየሱስ
ነፍሴ በርሱ አረፈች በሰላሙ ንጉስ
2.
አሥራ ሁለት ዓመት በደም ጐርፍ ረስርሼ
ጤናዬ ሳይመለስ ገንዘቤን ከስክሼ
ጤና ፈውስ አገኘሁ ቀሚሱን ዳስሼ
}x2ይኸው ተመስገን አልኩ ፊትህ ተጐንብሼ
ተመስገን አምላኬ ጤና ሰጥተኸኛል
ከሰቀቀን ሕይወት ነፃ አውጥተኸኛል
3.
ሰላሣ ስምንት ዓመት በአልጋ ላይ ተኝቼ
በወገን በዘመድ በሰው ተረስቼ
የናዝሬቱ ኢየሱስ ከስራቴ ፈታኝ
አልጋህን ተሸክመህ ተነሳ ሂድ አለኝ/2/
ከስራቴ ፈታኝ የናዝሬቱ ኢየሱስ
ክብርና ምሥጋና ይኸው ላንተ ይድረስ
4.
በምንዝር ተይዤ ልገደል ስወሰድ
ተፈርዶብኝ ልሞት ከዚህ ዓለም ልወገድ
በድንጋይ ከመወገር ኢየሱስ አዳነኝ
ኃጢአት እንዳልሠራ መክሮ ነፃ አወጣኝ /2/
ውዱ መድኃኒቴ የሱስ የኔ ጌታ
የልቤ ማረፊያ የነፍሴ መከታ
5.
ፍቅሩ ፍፁምና እጅግ ጥልቅ የሆነው
ተጠጋው ወገኔ ጥላ ማረፊያ ነው
ጭንቀት አበሳህን የሱስ ያውቅልሃል
ሸክምህን አራግፎ ሰላም ይሰጥሃል /2/
ሰላም ሰጥተኸናል ነፍሳችን ተጨንቃ
ተመስገን ተባረክ የሰላም አለቃ