ወደ መነሻ / Back to Home
መዝሙር #98 / Song #98

በመከራም ቢሆን ምሥጋና

english translation

ምድብ / Category: ምስጋና / Praise
ደራሲ / Author: unknown
ዓመት / Year: 2025
👁️ Views: 2
በፈተናም ቢሆን ምሥጋና
የከንፈሬ ፍሬ ለኢየሱስ ይገባዋልና
1.
እንዳልሆነ ሆኖ ኑሮ ብታይህም
እግዚአብሔር የተወህ መስሎ ቢስማህም
ማመስገን አትርሳ በፈተናህ ጊዜ
ክብር ለእርሱ ስተሰጥ ይጠፋል ትካዜ
2.
መላ ሁሉ ጠፍቶህ ግራ ስትጋባ
ወዳጅ ዘመድ ርቆህ ሆነህ ረዳት አልባ
ተስፋህን አትቁረጥ ወንድሜ አትስጋ
በምሥጋና መንፈስ ቅረብ ኢየሱስ ጋ
3.
ለሁሉም ጊዜ አለው ሁሉም ነገር ያልፋል
ደስታም ቢሆን ሀዘን ቀንም ይለወጣል
ሀብትና ሞገስም አንድ ቀን ይመጣል
ጊዜና ዕድል ግን ከአንዱ ያገናኛል
4.
በመከራ ጊዜ ማመስገን እንድንችል
ዓለምን በእምነት አሸንፈን በድል
በሚጣፍጥ ሆነ በሚመረው ነገር
አመስጋኝ እንድንሆን እርዳን እግዚአብሔር
100%
100%