ወደ መነሻ / Back to Home
መዝሙር #150 / Song #150

ከእንግዲህስ ወዲህ ምፃቱን እሰብካለሁ

english translation

ምድብ / Category: ምስጋና / Praise
ደራሲ / Author: unknown
ዓመት / Year: 2025
👁️ Views: 1
ከእንግዲህስ ወዲህ ምፃቱን እሰብካለሁ
ሰማያዊ አምላክ ይመጣል አውቃለሁ
የመከሩ ጌታ ማጭዱን ይሰዳል
የጐመራው እሸት ወደ ጐተራው ይከተዋል
1.
ከፀሐይ መውጫ ለሚመጣው
ለልዑልሽ መንገዱን ጥረጊ
እባክሽ ጽዮን ሆይ
ተነሺና አብሪ
2.
በደመና ላይ ተቀምጦ
በደማቅ ብርሃን አሸብርቆ
የወርቅ አክሊል ደፍቶ
ንጉሥሽ ይመጣል
3.
ወደ በጉ ሠርግ ለመግባት
ታላቁን ድግስ ለመብላት
ልብሳቸውን የሚያጥቡ
ብፁወን ቅዱሳን ናቸው
4.
ሀሌሉያ ሀሌሉያ
እልል እልል እንላለን
ባዲስቷ ምድር
ምሥጋና እንሰዋለን
100%
100%