የአምላክ ዋጋው ምሥጋና ነው ( 2)
ጨለማን ሌሊት ብርሃን ሲያደርገው
ተራራን ንዶ ሲያደላድለው
ሌላ ምን አለ የምንከፍለው?
1.
ምድር ሞላዋ ሁሉ የእርሱ
ሰማየ ሰማያት ባሕር የብሱ
እርሱን የሚያረካው ምን አለንና?
ሌላ ከአፋችን ምሥጋና
2.
የሞተን ተስፋ ኃይሉን ሲያድስ
የምርኮን አጥር ሲያፈራርስ
ሕዝቡን በእሣት ሲያሻግረው
ሌላ ምን አለ የምንከፍለው?
3.
የእንባውን ፍሬ ጠላት ሲያየው
ዘሩን በደስታ ሲሸከመው
ጠላት ከማዶ ሆዱ ሲደብን
የጌታ ዋጋው ተመስገን
4.
የዋይታን ሌሊት ሲያነጋጋው
ልቅሶን በደስታ ሲለውጠው
የዛለውን ልብ ሲያበረታው
ጌታ ተመስገን ብቻ ነው