1.
የጠላቴን እራስ ቀጥቅጠህ ከመጋጋው እኔን ነጥቀህ
ቅዱስ ደምህን አፍስሰህ ለሙት ልጅህ ሕይወት ሰጥተህ
ታላቁን መዳን፡ ድኛለሁ አሁንም መጽናት፡ አሻለሁ
በጊዜውም አለጊዜውም በስምህ ጸንቼ ቆሜ
ፊትህን ለማየት እጓጓለሁ እሩጫዬን ፈጽሜ
ስለዚህ ፈቃድህን ይሁንልኝ ውድ አባቴ
በሰላም በጤና አድርሰኝ ከቤቴ።
2.
ስቅበዘበዝ መክረኸኛል ስተክዝ አፅናንተኸኛል
ባቆስልህም ወደኸኛል ዘወትር ተሸክመኸኛል
እስከዛሬ ችለኸኛል ቅዱስ ሥምህ አቁሞኛል
3.
ዘወትር በሁሉም ስፍራ አንተን ልምሰል አንተን ልፍራ
ከዓለም አድርገኝ ልዩ በእኔም ሕይወት አንተን ይዩ
ሥጋዬን ለዓለም ሰቅዬ ልጓዝ አንተን ተከትዬ
4.
በድካም ሕይወቴ ላልቶ አካሄዴም ተበላሽቶ
ቅዱስ ሥምህ አንዳይሰደብ አደራ ልጅህን አስብ
እስክትመጣልኝ በክብር አንተን አስከብሬ ልኑር
5.
በከፍታም በዝቅታም በሀዘንም በደስታም
ሳልደናገር በእርጋታ በፈተናም ሳልረታ
በትጋት ፀንቼ በእምነት ፊትህን ልየው በክበር