እንናገራለን ትንሣኤውን
ለኛ ሲል በመስቀል የሞተውን
የናዝሬቱ ኢየሱስ አዳኙን
1.
ከድቅድቅ ጨለማ ወደ ብርሃን
ከዘላአለም ሞት ያወጣንን
ሕይወት አግኝተናል በየሱስ ሞት
እንመሠክራለን በድፍረት
2.
ቀንበራችንን ሁሉ ሠባብሮ
መንገዳችንን ሁሉ አሳምሮ
የቀድሞው ሥማችንን ቀይሮ
እንደገና አቆመን ዘንድሮ
3.
ከፊት ለፊታችን ተራራ
ከጐናችን ደግሞ መከራ
በሞት አዋጅ ዙሪያችን ተከበን
የናዝሬቱ ኢየሱስ አወጣን
4.
በምድርና በሠማይ መኸከል
ሰለኃጢአታችን በመንጠልጠል
በቀራኒዮ ፍቅሩን ገልጾልናል
መዳናችን ያኔ ተረጋግጧል
5.
አንተ እረኛ በጐቹን ጠብቅ
እንዳይበተኑ ለአራዊት መብል
በምን ቸገረኝ ቸል ብለህ ሳለህ
ከተበተኑ /ከተነጠቁ ትጠየቃለህ
6.
ወይ አንተ አልገባህ የሚገቡትን ትከለክላለህ
ፃዲቃንን ሁሉ በክፉ ሥራ ትመልሳለህ
}2xከላይ እግዚአብሔር ይጠይቅሃል
አቤል ወንድምህ ወዴት ነው ይልሃል
7.
የደከመውን የቦዘነውን አላጸናህም
የታመመውን የተሠበረውን አልጠገንከውም
}2xስለዚህ እግዚአብሔር ከላይ ይጮኸል
ክፉ እረኛ ወዮልህ ይልሃል
8.
በምድር ያሉትን ጣኦታትን ሁሉ ትፀየፋለህ
መቅደሱን በመዝረፍ ከፍ ያለውን ጌታ ታሳፍራለህ
}2xበአንተ ሠበብ የአምላክህን ስም
በሠማይ ያለውን ታሰድባለህ
9.
ልወድቅ ያለውን ዘንበል ያለውን ቤት አይተህ አልፈሃል
በምላስህ ጦር ወንድምህን ወግተህ አስመርረሃል
}2xእግዚአብሔር አምላክ ይገስጽሃል
ከክፉ ሥራህ ተመለስ ይልሃል