ኑ ወደ ጌታ የሱስ አርሱ እንዲያሳርፋችሁ
ታማኝ ነውና ጌታ በተናገረው ቃሉ
የሚያስጨንቃችሁን ሁሉ በእርሱ ላይ ጣሉ
1.
በሰማይ የሚበሩትን ወፎችን የሚመግብ
ሳይዘሩና ሳያጭዱ ሳይደክሙ የሚያጠግብ
የሰማይ አባታችሁ ለእናንተ አያንስምና
በመተማመን ጥሩት አያሳፍርምና
2.
ምንስ እንበላለን ምንስ እንለብሳለን
በማለት አታስቡ እንዴት እንሆናለን
ጌታን አስቡት እንጂ እምነት አይጉደላችሁ
አምላክ እንደሌላቸው አትሁኑ እባካችሁ
3.
የሚያስፈልጋችሁን ሁሉ ያውቃልና
ከእናንተ በላይ ስለ እናንተ ያስባልና
ትካዜአችሁን በእርሱ ላይ ጥላችሁ እረፉ
እንጂ በራስ ማስተዋል ከቶ አትደገፉ
4.
በመጀመሪያ የጌታን ፅድቁንና መግንሥቱን
ተግታችሁ ብትፈልጉ በሰማይ የሆነውን
ሁሉን ያትረፈርፋል ያበዛላችሁማል
በላይ ያለውን ብትቩ ሌላ ይጨመርላችኋል