ወደ መነሻ / Back to Home
መዝሙር #194d / Song #194d

ምሥጋና ምሥጋና ክብር (2)

english translation

ምድብ / Category: ምስጋና / Praise
ደራሲ / Author:  አገኘሁ ይደግ
ዓመት / Year: 2025
👁️ Views: 3
ምሥጋና ምሥጋና ክብር (2)
ለአምላካችን ለእግዚአብሔር (2)
1.
ኃጥያተኞች ሳለን እግዚአብሔር አሰበን
ከፋንዲያ ላይም ከፍ ከፍ አረገን
በሕይወት መዝገብ ላይ ሥማችንን ጻፈው
የዘለዓለም አምላክ ምሥጋና ይድረሰው
በሕይወት መዝገብ ላይ ሥማችንን ጻፈው
የናዝሬቱ ኢየሱስ ምሥጋና ይድረሰው።
2.
ኢየሱስ እረኛችን ጠባቂያችን ሆኗል
በሞት ጥላም ብንሄድ ምንድን ያስፈራናል?
በለመለምው መስክ በእረፍት ውኃ ዘንድ
ሁሌ ይመራናል ወደ እውነት መንገድ። (2)
3.
አዕምሮን የሚያልፍ ሰላሙን ሰጥቶናል
በጌታ በኢየሱስ ሁሌ ደስ ይለናል
ምድር ብትናውጥ አንዳች አንሆንም
የመረጠን አምላክ/ኢየሱስ/ፈጽሞ አይተወንም (2)
4.
እግዚአብሔር ከላይ በድንቅ ጐብኝቶናል
በመንፈስ ቅዱስ ኃይል በእሳት አጥምቆናል
በመከራም ጊዜ እንደሰታለን
እንደ ዘንባባ ዛፍ እንለመልማለን
በመከራም ጊዜ እንደሰታለን
በሽምግልናችን እንለመልማለን።
100%
100%