ወደ መነሻ / Back to Home
መዝሙር #173 / Song #173

ፀባዬን አይቶ እኔን ያልራቀኝ

english translation

ምድብ / Category: ምስጋና / Praise
ደራሲ / Author: unknown
ዓመት / Year: 2025
👁️ Views: 1
ፀባዬን አይቶ እኔን ያልራቀኝ
እንደበደሌ ያልፈረደብኝ
ጌታ ኢየሱስ ለዘላለም ይክበርልኝ
አሜን ይንገሥልኝ
1.
ሰው እንደሚያይ አያይም በቶሎ አይፈርድም
ችግሬን ስለሚያውቅ አጋልጦ አይሰጠኝም
ያስተካክለዋል ህይወቴ ሲጣማም
በእኔ አለመታዘዝ ልተወኝ አይፈቅድም
2.
ከግብጽ እንድወጣ ከዓለም እሥራት
ቃል እንደገባልኝ ጽዮንን እንዳያት
በበረሃ ጉዞ ልተወኝ አይወድም
ጌታዬ ታማኝ ነው እስከዘላለም
3.
ስደክም ደግፎኝ ሳጠፋ ሚቆጣኝ
በኃጢያት እንዳልወድቅ የሚንከባከበኝ
ትከሻዬ ሲዝል ሸክሜን የሚያግዘኝ
በዘውትር ጉዞዬ አለሁ የሚለኝ
4.
ስበድል ሳሳዝን ሰልችቶ አልተወኝ
በአመጽ ኑሮዬ ቀስፎ አልጣለኝ
በእኔ ፋንታ ሞቶ ነፃ ያወጣኝ
የዛላለም አባት ጌታ ይክበርልኝ
አሜን ይክበር
100%
100%