ወደ መነሻ / Back to Home
መዝሙር #161 / Song #161

በዓለም ዳርቻ ሁሉ እንድንመሰክር

english translation

ምድብ / Category: ምስጋና / Praise
ደራሲ / Author: unknown
ዓመት / Year: 2025
👁️ Views: 1
በዓለም ዳርቻ ሁሉ እንድንመሰክር
ኃያልነትህን ደግሞ እንድንናገር
እንድንወጣው ታላቁን አደራ
ያ ብዙ አፅናኙ መንፈስ ቅዱስ ይምጣ
1.
አንተ መንፈስ ቅዱስ ሆይ /2X/
ና ጉልበታችንን አፅና /4X/
2.
ተስፋ ለምንቆርጥ በየምክንያቱ
መታመን ያቃተን ሁነናል አቤቱ
በክፉም በደጉም ባንተ እንድንጸና
መንፈስ ቅዱስህን ላክ ይረዳናልና
3.
አንተ መንፈስ ቅዱስ ሆይ /2X/
ና እምነታችንን አፅና/4X/
4.
ሌላውን ለመገሰጽ ራሳች ፈጣን ነን
መንፈሳችንማ ዓይናችን እውር ነው
ራሳችንን ሳናይ ብዙ ተጐድተናል
መንፈስ ቅዱስን ላክ ያስችለናልና
5.
አንተ መንፈስ ቅዱስ ሆይ/2X/
ና ህይወታችንን አፅና/4X/
ና እምነታችንን አፅና/2X/
ና ጉልበታችንን አፅና/4X/
100%
100%