ወደ መነሻ / Back to Home
መዝሙር #114 / Song #114

አንተ የሰጠኸን በረከት

english translation

ምድብ / Category: ምስጋና / Praise
ደራሲ / Author: unknown
ዓመት / Year: 2025
👁️ Views: 1
ለጉዞአችን የሚሆነን መብራት
}2xህግህ ነው ለእኛ መመሪያ
ከክፉ ሁሉ መጠለያ
1.
ዱካህ ከቶ እንዳይጠፋብን
ሁሌ የሚያሳየኝ መንገዱን
ሰጠተኸናል ጌታ በረከት
ክብር ይገባሃል የኛ አባት
2.
ብዙ መጽሐፍት ሲቀየሩ
ደግሞም የሰው ህጐች ሲሻሩ
የእግዚአብሔር ቃል ግን ፀንቶ ይኖራል
አይሰለችም ዛሬም ይመራናል
3.
ሰማይና ምድር ሁሉም ያልፋል
የጌታ ቃል ግን ፀንቶ ይኖራል
ሐዋሪያቶችን በድንቅ የመራ
እስከዛሬም አለ ከኛ ጋራ
4.
በቤትህ ለብዙ ዓመታት ኖረን
ሳናስተውል ቀርተን ቃልህን
ከወጉህ ጋር አብረን እንዳንጠፋ
ማስተዋል ስጠን የኛ ተስፋ
5.
እምነቴን አበርታ ጌታ/2X/
እምነቴን አበርታ የሱስ/2X/
ወጀቡ ሲናወጥ ያኔ እመነቴ እንዳይጠፋ
ማዕበሉ ሲነሳ ደግሞ ትጥቄ እንዳይፈታ
እምነቴን አበርታ ጌታ/2X/
6.
ካንተጋራ ጉዞ የሱስ እጅጉን ይመቻል
በባህር ላይ ደግሞ ስታዝ መራመድ ይቻላል
ግን ፈርቼ ስጠራጠር አልፎም ስመራመር
ባንተ ያለኝ እምነት ጠፍቶ ሰጥሜ እንዳልቀር
7.
በሕይወት ማዕበል ወደብ ምንም ባያቋርጥ
ሁኔታው ሁሉ ቢመስል ተስፋ የሚያስቆርጥ
ማዕበል ሆነ ወደብ ነፋስ የሚታዘዙልህ
እምነቴን አበርታ ልወቅ ከእኔ ጋር እንዳለህ
8.
በዚህ ክፉ ዓለም ስኖር ስወጣና ስወርድ
ስንዴነቴ ቀርቶ ጭራሽ እንዳልሆን እንክርዳድ
የእምነቴ ብርሃን ጠፍቶ ጨለማ እንዳይውጠኝ
ዕለት ዕለት አንተም እኔን አይዞህ ንቃ በለኝ
9.
ሀብትም ቢሆን ክብር ዝና ወይም ብልጽግና
ማጣት መንጣት ውርደት ቢሆን ወይም ጉስቁልና
እየተፈራረቁብኝ ሁሉም በየተራ
ካንተ ተለይቼ እንዳልሄድ ጠብቀኝ አደራ
100%
100%