ወደ መነሻ / Back to Home
መዝሙር #244d / Song #244d

ድሉ የጌታችን ነው

english translation

ምድብ / Category: ምስጋና / Praise
ደራሲ / Author: unknown
ዓመት / Year: 2025
👁️ Views: 3
ድሉ የጌታችን ነው ድሉ ያምላካችን ነው ድሉ
ድሉ የጌታችን ነው
ጠላትን ረገጠ አርነት አወጀ
ለኛ ለልጆቹ ማረፊያ አዘጋጀ
ድሉ ያምላካችን ነው
1.
ከዲያቢሎስ ወጥመድ ልንድን
በጌታችን ብርታት ተሞላን
እንግዲህ እንገስግስ አንተኛ
የኢየሱስ ነን እኛ
2.
እስራኤልን ከግብፅ ያወጣ
ፈርኦንን በባህር የቀጣ
ይህን ታዳጊ አምላክ አምነናል
በድል ይመራናል
3.
ኢያሱ ጌዲዮንና ዳዊት
አብርሃምና ሙሴ ያለፉት
የእምነትና የጦር አርበኞች
የድል ምሳሌዎች
4.
የጠላት ማሽካካት ድንፋታ
የሰልፍ የጦር ብዛት ጋጋታ
ለሃያሉ ኢየሱስ ምኑ ነው
ሁሉም በእጁ ነው
100%
100%