ዛሬም በምስጋና ነገም በምስጋና
ሁሌም በምስጋና ልቅረብ እንደገና /2/
1.
በጨነቀኝ ጊዜ እርሱን ጠራሁኝ
በፊቱም አነባው አባባ እያልኩኝ
ጩኸቴንም ሰምቶ ከተፍ አለልኝ
እንባዬን ጠራርጐ ደግፎ አቆመኝ
2.
የተከተለኝን የፈርኦን ሠራዊት
በባሕር አስጥሞ ሆነልኝ መድኃኒት
በድንቅ እየመራኝ በቀን በሌሊት
ውለታውን ለመግለጽ የለኝ አንደበት
3.
ባዶ ማድጋዬን በዘይት ሞልቶታል
ተራራዬን ንዶ ሜዳ አድርጐታል
ከጠየቅኩት በላይ አድርጐልኛል
መሻቴንም ሁሉ ፈጽሞልኛል
4.
ምከፍለው የለኝም ለውለታው ምላሽ
ታዲያ ምንስ ልስጠው ለእንባዬ አባሽ
ዛሬም ነገም ሁሌም ዳግም እንደገና
ለዘላለም አለም ይድረሰው ምስጋና /2/