የአምላኬ ውለታው ብዙ ነውና
ተስፋዬን አደሰው ምርኮዬን መለሰው
ለመድኃኒቴ አምላክ ምሥጋና ይድረሰው/2X/
1.
አምላኬ ከጐኔ ሆኖ ባይረዳኝ
ጠላቴ በብዙ እኔን ቢያሰቃየኝ
ጌታዬ ይመስገን የአምላክ ጥበቃው
ለአኔም በዛልኝ ምሥጋና ይድረሰው/2X/
2.
እኔም እንደዳዊት ብቻዬን ሆኜ
አይኖቼን አነሳሁ ወደ አዳኙ
ረድኤትን ይዞ ከተፍ አለልኝ
ፈውስ ቤቴን ሞላ ጌታ ይክበርልኝ/2X/
3.
ዛሬ በምሥጋና ቅኔ ተሞላሁ
ጐልበቴም በረታ ኃይልን አገኘሁ
የአምላኬን ሥራ ስንቱን ልናገር
ከቁጥር በላይ ነው ስንቱን ልዘርዝር/2X/
4.
ኃይሌ በድካሜ ይኸው ተፈፀመ
የደረቀው ህይወቴን አለመለመ
ጌታዬ በእኔ ላይ ዓላማ አለው
ጥንትም ቢሆን ዛሬ ሁሉ ለበጐ ነው/2X/
5.
ባህሩንም ከፍሎ ያሻገራቸውን
በምድረበዳ ውስጥ የመገባቸውን
እኛና ቤታችን እናመልከዋለን
እንደ እያሱ ምርጫ እንመርጠዋለን
6.
እናንተስ ማንን መረጣችሁ ዛሬ
እግ/ርን ወይስ የዓለምን ኩነኔ
በለብታ ሕይወት መኖር አይመችም
በመንታ ልብ ሆኖ መቆም አይቻልም
7.
የፈርኦንን ቤት ታላቅነት ጠልቶ
የእግ/ርን ሕዝብ መሰቃየት አይቶ
ወዶ እንደመረጠ ስቃይ መቀበልን
እንደ ሙሴ ምርጫ እኛም እግ/ርን
8.
በ12 ጥማድ ሲያርስ የነበረው
በብዙ አገልጋዮች በጣም የከበረው
ያንን ሁሉ ትቶ ወዶ እንደመረጠው
እኛም እንደ ኤልሣዕ ምርጫችን ጌታ ነው
9.
በአለም ተንከራቶ እርካታን ስላጣ
የዚህ ዓለም ኑሮ ሰለማያዋጣ
የአባቱን ቤት ተድላ ወዶ እንደመረጠው
እኛም እንደዚያ ልጅ ምርጫችን የሱስ ነው