ወደ መነሻ / Back to Home
መዝሙር #5 / Song #5

አገራችን ሰማይ ነው እዚህ ምንም የለን

english translation

ምድብ / Category: ምስጋና / Praise
ደራሲ / Author: unknown
ዓመት / Year: 2025
👁️ Views: 6
አገራችን ሰማይ ነው እዚህ ምንም የለን
ጌታ ወዶና ፈቅዶ እርሱ አዘጋጀልን
በእጅ ያልተሰራ ህንፃ በሰማይ ስላለን
ከዚህ ዓለም መከራ ሄደን እናርፋለን
1.
ጌታ ወዶና ፈቅዶ እርሱ አዘጋጀልን
በእጅ ያልተሰራ ህንፃ በሰማይ ስላለን
ከዚህ ዓለም መከራ ሄደን እናርፋለን
2.
እኛስ ታድለናል በርሱ የተመረጥን
ከሚጠፋው ዓለም ለህይወት የለየን
እርሱ አባታችን ንጉሣችን ሆኗል
ለሰማይ ቤታችን እርሱ ያበቃናል
3.
ለቅሶ ዋይታ ችግር የለም በዚያ ቦታ
በህይወት መኖር ነው ዘላለም በደስታ
መከፋፈል የለም ወይም ሀዘን ችግር
ሥራችን ይሆናል ጧት ማታ መዘመር
4.
በሮቿ ሁልጊዜ ከቶ አይዘጉም
ሌቦች ወንበዴዎች ከዚያ አይገኙም
የሚያውከን ነገር በምድር ይቀራል
በጉ ከኛ ጋራ ለዘላለም ያድራል
5.
ሰላምና ደስታ ሁሌ ሚገኝባት
የነገሥታት ንጉስ ገዢ የሆነባት
የኛ የዕረፍት አገር ጌታ የቀደሳት
መኖሪያ ቤታችን ኢየሩሳሌም ናት\n\n
100%
100%